Ana SayfaMealler › M.Sadiq and M.Sani Habib
MS

M.Sadiq and M.Sani Habib

M.Sadiq and M.Sani Habib
M.Sadiq and M.Sani Habib meali ile okumaya başla
Araf 1 / 206
1
አ.ለ.መ.ሰ (አሊፍ፤ ላም ፤ሚም፤ ሷድ)፡፡
M.Sadiq 7:1
2
(ይህ) ወደ አንተ የተወረደ መጽሐፍ ነው፡፡ በደረትህም ውስጥ ከእርሱ ጭንቀት አይኑር፡፡ (የተወረደውም) በእርሱ ልታስፈራራበትና ለምእምናን መገሠጫ እንዲኾን ነው፡፡
M.Sadiq 7:2
3
ከጌታችሁ ወደእናንተ የተወረደውን ተከተሉ፡፡ ከአላህም ሌላ ረዳቶችን አትከተሉ፡፡ ጥቂትን ብቻ ትገሰጻላችሁ፡፡
M.Sadiq 7:3
4
ከከተማም ልናጠፋት የሻነው ወዲያውም ብርቱ ቅጣታችን ሌሊት ወይም ቀን እነርሱ በቀትር አርፈው ሳሉ የመጣባቸው ብዙ ናቸው፡፡
M.Sadiq 7:4
5
ቅጣታችንም በመጣባቸው ጊዜ «ጸሎታቸው እኛ በደለኞች ነበርን» ከማለት በቀር ሌላ አልነበረም፡፡
M.Sadiq 7:5
6
እነዚያንም ወደነሱ የተላከባቸውን (ሕዝቦች) በእርግጥ መልክተኞቹንም እንጠይቃለን፡፡
M.Sadiq 7:6
7
በእነርሱም ላይ (የነበሩበትን ሁሉ) ከዕውቀት ጋር በእርግጥ እንተርክላቸዋለን፡፡ የራቅንም አልነበርንም፡፡
M.Sadiq 7:7
8
ትክክለኛውም ሚዛን የዚያን ቀን ነው፡፡ ሚዛኖቻቸው የከበዱላቸው ሰዎችም እነዚያ እነርሱ የፈለጉትን ያገኙ ናቸው፡፡
M.Sadiq 7:8
9
ሚዛኖቻቸው የቀለሉባቸው ሰዎችም እነዚያ እነርሱ ተአምራቶቻችንን ይክዱ በነበሩት ምክንያት ነፍሶቻቸውን ያከሰሩ ናቸው፡፡
M.Sadiq 7:9
10
በምድርም ላይ በእርግጥ አስመቸናችሁ፡፡ በእርሷም ላይ ለናንተ መኖሪያዎችን አደረግንላችሁ፤ ምስጋናችሁ በጣም ጥቂት ነው፡፡
M.Sadiq 7:10
11
በእርግጥም ፈጠርናችሁ፡፡ ከዚያም ቀረጽናችሁ፡፡ ከዚያም ለመላእክቶች «ለአዳም ስገዱ» አልን፡፡ ወዲያውም ሰገዱ፡፡ ኢብሊስ (ዲያብሎስ) ሲቀር ከሰጋጆቹ አልኾነም፡፡
M.Sadiq 7:11
12
(አላህ) «ባዘዝኩህ ጊዜ ከመስገድ ምን ከለከለህ» አለው፡፡ «እኔ ከርሱ የበለጥኩ ነኝ፡፡ ከእሳት ፈጠርከኝ፡፡ እርሱን ግን ከጭቃ ፈጠርከው» አለ፡፡
M.Sadiq 7:12
13
ከእርሷ ውረድ፤ በእርሷ ውስጥ ልትኮራ አይገባህምና፡፡ ውጣም አንተ ከወራዶቹ ነህና አለው፡፡
M.Sadiq 7:13
14
«እስከሚቀሰቀሱበት ቀን ድረስ አቆየኝ» አለ፡፡
M.Sadiq 7:14
15
፡-አንተ ከሚቆዩት ነህ አለው፡፡
M.Sadiq 7:15
16
«ስለአጠመምከኝም ለእነርሱ በቀጥተኛው መንገድ ላይ በእርግጥ እቀመጥባቸዋለሁ» አለ፡፡
M.Sadiq 7:16
17
«ከዚያም ከስተፊቶቻቸው ከኋላቸውም ከቀኞቻቸውም ከግራዎቻቸውም በእርግጥ እመጣባቸዋለሁ፡፡ አብዛኞቻቸውንም አመስጋኞች ኾነው አታገኛቸውም» (አለ)፡፡
M.Sadiq 7:17
18
«የተጠላህ ብራሪ ስትኾን ከእርሷ ውጣ፡፡ ከእነርሱ የተከተለህ ከእናንተ ከመላችሁም ገሀነምን በእርግጥ እሞላታለሁ» አለው፡፡
M.Sadiq 7:18
19
«አዳም ሆይ! አንተም ሚስትህም በገነት ተቀመጡ፡፡ ከሻችሁትም ስፍራ ብሉ፡፡ ግን ይህችን ዛፍ አትቅረቡ፡፡ (ራሳቸውን) ከሚበድሉት ትኾናላችሁና» (አላቸው)፡፡
M.Sadiq 7:19
20
ሰይጣንም ከሐፍረተ ገላቸው የተሸሸገውን ለእነርሱ ሊገልጽባቸው በድብቅ ንግግር ጎተጎታቸው፡፡ «ጌታችሁም መልኣኮች እንዳትኾኑ ወይም ከዘላለም ነዋሪዎች እንዳትኾኑ እንጂ ከዚህች ዛፍ አልከለከላችሁም» አላቸው፡፡
M.Sadiq 7:20
21
«እኔ ለእናንተ በእርግጥ ከሚመክሩዋችሁ ነኝ» ሲልም አማለላቸው፡፡
M.Sadiq 7:21
22
በማታለልም አዋረዳቸው፡፡ ከዛፊቱም በቀመሱ ጊዜ ኀፍረተ ገላቸው ለሁለቱም ተገለጠችላቸው፡፡ ከገነት ቅጠልም በላያቸው ላይ ይደርቱ ጀመር፡፡ ጌታቸውም «ከዚህ ዛፍ አልከለከልኋችሁምን ሰይጣንም ለእናንተ ግልጽ ጠላት ነው አላልኳችሁምን» ሲል ጠራቸው፡፡
M.Sadiq 7:22
23
«ጌታችን ሆይ! ነፍሶቻችንን በደልን፡፡ ለእኛ ባትምር ባታዝንልንም በእርግጥ ከከሳሪዎቹ እንኾናለን» አሉ፡፡
M.Sadiq 7:23
24
(አላህ) « ከፊላችሁ ለከፊሉ ጠላት ሲኾን ውረዱ፡፡ ለእናንተም በምድር ላይ እስከ ተወሰነ ጊዜ ድረስ መርጊያና መጠቀሚያ አላችሁ» አላቸው፡፡
M.Sadiq 7:24
25
«በእርሷ ላይ ትኖራላችሁ፡፡ በእርሷም ላይ ትሞታላችሁ፡፡ ከእርሷም ውስጥ ትወጣላችሁ» አላቸው፡፡
M.Sadiq 7:25
26
የአዳም ልጆች ሆይ! ኀፍረተ ገላችሁን የሚሸሽግን ልብስ ጌጥንም በእርግጥ በናንተ ላይ አወረድን፡፡ አላህን የመፍራትም ልብስ ይህ የተሻለ ነው፡፡ ይህ ከአላህ ታምራቶች ነው፡፡ ይገሠጹ ዘንድ (አወረደላቸው)፡፡
M.Sadiq 7:26
27
የአዳም ልጆች ሆይ! ሰይጣን አባትና እናታችሁን ኀፍረተ ገላቸውን ሊያሳያቸው ልብሶቻቸውን ከነሱ የገፈፋቸው ሲኾን ከገነት እንዳወጣቸው ሁሉ እናንተን አይሞክራችሁ፡፡ እነሆ እርሱ ከነሰራዊቱ ከማታዩዋቸው ስፍራ ያዩዋችኋልና፡፡ እኛ ሰይጣናትን ለእነዚያ ለማያምኑት ወዳጆች አድርገናል፡፡
M.Sadiq 7:27
28
መጥፎንም ሥራ በሠሩ ጊዜ በእርሷ ላይ አባቶቻችንን አገኘን አላህም በእርሷ አዞናል ይላሉ፡፡ «አላህ በመጥፎ ነገር አያዝም፡፡ በአላህ ላይ የማታውቁትን ትናገራላችሁን» በላቸው፡፡
M.Sadiq 7:28
29
ጌታዬ በማስተካከል አዘዘ፡፡ በየመስጊዱም ዘንድ ፊቶቻችሁን (እርሱን ለመገዛት) አስተካክሉ፡፡ ሃይማኖትንም ለእርሱ ፍጹም አድርጋችሁ ተገዙት፡፡ እንደጀመራችሁ ትመለሳላችሁ» በላቸው፡፡
M.Sadiq 7:29
30
ከፊሉን ወደ ቅን መንገድ መራ፡፡ ከፊሎቹም በእነሱ ላይ ጥመት ተረጋግጦባቸዋል፡፡ እነርሱ ሰይጣናትን ከአላህ ሌላ ረዳቶች አድርገው ይዘዋልና፡፡ እነርሱም (ቅኑን መንገድ) የተመራን ነን ብለው ያስባሉ፡፡
M.Sadiq 7:30