Ana SayfaMealler › M.Sadiq and M.Sani Habib
MS

M.Sadiq and M.Sani Habib

M.Sadiq and M.Sani Habib
M.Sadiq and M.Sani Habib meali ile okumaya başla
Necm 1 / 62
1
በኮከብ እምላለሁ በወደቀ (በገባ) ጊዜ፡፡
M.Sadiq 53:1
2
ነቢያችሁ (ሙሐመድ) አልተሳሳተም፤ አልጠመመምም፡፡
M.Sadiq 53:2
3
ከልብ ወለድም አይናገርም፡፡
M.Sadiq 53:3
4
እርሱ (ንግግሩ) የሚወርረድ ራእይ እንጅ ሌላ አይደለም፡፡
M.Sadiq 53:4
5
ኀይሎቹ ብርቱው (መልአክ) አስተማረው፡፡
M.Sadiq 53:5
6
የዕውቀት ባለቤት የኾነው (አስተማረው፤ በተፈጥሮ ቅርጹ ኾኖ በአየር ላይ) ተደላደለም፡፡
M.Sadiq 53:6
7
እርሱ በላይኛው አድማስ ኾኖ፡፡
M.Sadiq 53:7
8
ከዚያም ቀረበ፤ ወረደም፡፡
M.Sadiq 53:8
9
(ከእርሱ) የሁለት ደጋኖች ጫፍ ያህል ወይም (ከዚህ) ይበልጥ የቀረበ ኾነም፡፡
M.Sadiq 53:9
10
ወደ ባሪያውም (አላህ) ያወረደውን አወረደ፡፡
M.Sadiq 53:10
11
(ነቢዩም በዓይኑ) ያየውን ልቡ አልዋሸም፡፡
M.Sadiq 53:11
12
ታዲያ በሚያየው ላይ ትከራከሩታላችሁን?
M.Sadiq 53:12
13
በሌላይቱም መውረድ ጊዜ በእርግጥ አይቶታል፡፡
M.Sadiq 53:13
14
በመጨረሻይቱ ቁርቁራ አጠገብ፤
M.Sadiq 53:14
15
እርሷ ዘንድ መኖሪያይቱ ገነት ያለች ስትኾን፡፡
M.Sadiq 53:15
16
ቁርቁራይቱን የሚሸፍን ነገር በሚሸፍናት ጊዜ (አየው)፡፡
M.Sadiq 53:16
17
ዓይኑ (ካየው) አልተዘነበለም፡፡ ወሰንም አላለፈም፡፡
M.Sadiq 53:17
18
ከጌታው ታምራቶች ታላላቆቹን በእርግጥ አየ፡፡
M.Sadiq 53:18
19
አል-ላትንና አል-ዑዛን አያችሁን?
M.Sadiq 53:19
20
ሦስተኛይቱንም አነስተኛዋን መናትን (አያችሁን? የምትግገዟቸው ኃይል አላቸውን?)
M.Sadiq 53:20
21
ለእናንተ ወንድ ለእርሱም ሴት (ልጅ) ይኖራልን?
M.Sadiq 53:21
22
ይህቺ ያን ጊዜ አድላዊ ክፍያ ናት፡፡
M.Sadiq 53:22
23
እነርሱ እናንተና አባቶቻችሁ (አማልክት ብላችሁ) የጠራችኋቸው ስሞች ብቻ እንጅ ምንም አይደሉም፡፡ አላህ በእርሷ (መግገዛት) ምንም ማስረጃ አላወረደም፡፡ ከጌታቸውም መምሪያ የመጣላቸው ሲኾኑ ጥርጣሬንና ነፍሶች የሚዘነበሉበትን እንጅ ሌላ አይከተሉም፡፡
M.Sadiq 53:23
24
ለሰው የተመኘው ሁሉ አለውን?
M.Sadiq 53:24
25
መጨረሻይቱም መጀመሪያይቱም (ዓለም) የአላህ ብቻ ናቸው፡፡
M.Sadiq 53:25
26
በሰማያት ውስጥ ካለ መልአክም ብዙዎች (ሊማለዱለት) ለሚሻውና ለሚወደው ሰው ከፈቀደ በኋላ ቢኾን እንጅ ምልጃቸው ምንም አትጠቅምም፡፡
M.Sadiq 53:26
27
እነዚያ በመጨረሻይቱ ዓለም የማያምኑት መላእክትን በሴት አጠራር ይጠራሉ፡፡
M.Sadiq 53:27
28
ለእነርሱም በእርሱ ምንም ዕውቀት የላቸውም፡፡ ጥርጣሬን እንጅ ሌላን አይከተሉም፡፡ ጥርጣሬም ከእውነት ምንም አያብቃቃም፡፡
M.Sadiq 53:28
29
ከግሣጼያችንም (ከቁርኣን) ከሸሸና አነስተኛይቱን ሕይወት እንጅ ሌላን ከማይሻ ሰው ዙር (ተወው)፡፡
M.Sadiq 53:29
30
ይህ (አነስተኛይቱን ሕይወት መምረጥ) ከዕውቀት ድካቸው ነው፡፡ ጌታህ እርሱ ከመንገዱ የተሳሳተውን በእርግጥ ዐዋቂ ነው፡፡ እርሱም የቀናውን ሰው ዐዋቂ ነው፡፡
M.Sadiq 53:30