Ana SayfaMealler › M.Sadiq and M.Sani Habib
MS

M.Sadiq and M.Sani Habib

M.Sadiq and M.Sani Habib
M.Sadiq and M.Sani Habib meali ile okumaya başla
Fetih 1 / 29
1
እኛ ላንተ ግልጽ የኾነን መክፈት ከፈትንልህ፡፡
M.Sadiq 48:1
2
አላህ ከኃጢአትህ ያለፈውንና የሚመጣውን ላንተ ሊምር ጸጋውንም ባንተ ላይ ሊሞላ ቀጥተኛውንም መንገድ ሊመራህ (ከፈተልህ)፡፡
M.Sadiq 48:2
3
አላህ ብርቱን እርዳታ ሊረዳህም (ከፈተልህ)፡፡
M.Sadiq 48:3
4
እርሱ ያ በምእምናን ልቦች ውስጥ ከእምነታቸው ጋር እምነትን ይጨምሩ ዘንድ እርጋታን ያወረደ ነው፡፡ ለአላህም የሰማያትና የምድር ሰራዊቶች አልሉት፡፡ አላህም ዐዋቂ ጥበበኛ ነው፡፡
M.Sadiq 48:4
5
ምእምናንንና ምእምናትን ከሥሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸውን ገነቶች በውስጣቸው ዘውታሪዎች ሲኾኑ ሊያገባቸው ከነርሱም ኃጢአቶቻቸውን ሊያብስላቸው (በትግል አዘዛቸው)፡፡ ይህም ከአላህ ዘንድ የኾነ ታላቅ ማግኘት ነው፡፡
M.Sadiq 48:5
6
በአላህም ክፉ ጥርጣሬን ተጠራጣሪዎቹን መናፍቃንና መናፍቃትን፣ ወንዶች አጋሪዎቻችንና ሴቶች አጋሪዎችንም ያሰቃይ ዘንድ (በትግል አዘዘ)፡፡ በእነርሱ ላይ ክፉ ከባቢ አለባቸው፡፡ በእነርሱም ላይ አላህ ተቆጣባቸው፡፡ ረገማቸውም፡፡ ለእነርሱም ገሀነምን አዘጋጀላቸው፡፡ መመለሻነትዋም ከፋች፡፡
M.Sadiq 48:6
7
ለአላህም የሰማያትና የምድር ሰራዊቶች አልሉት፡፡ አላህም አሸናፊ ጥበበኛ ነው፡፡
M.Sadiq 48:7
8
እኛ መስካሪ አብሳሪና አስፈራሪም አድርገን በእርግጥ ላክንህ፡፡
M.Sadiq 48:8
9
በአላህ ልታምኑ፣ በመልክተኛውም (ልታምኑ)፣ ልትረዱትም፣ ልታከብሩትም፣ (አላህን) በጧትና ከቀትር በኋላ ልታወድሱትም (ላክነው)፡፡
M.Sadiq 48:9
10
እነዚያ ቃል ኪዳን የሚጋቡህ ቃል ኪዳን የሚጋቡት አላህን ብቻ ነው፡፡ የአላህ እጅ (ኀይሉ) ከእጆቻቸው በላይ ነው፡፡ ያፈረሰም ሰው የሚያፈርሰው በነፍሱ ላይ ብቻ ነው፡፡ በእርሱ ላይ አላህን ቃል ኪዳን የተጋባበትን የሞላም ሰው ታላቅ ምንዳን በእርግጥ ይሰጠዋል፡፡
M.Sadiq 48:10
11
ከአዕራብ ሰዎች እነዚያ (ከዘመቻ) ወደ ኋላ የቀሩት ለአንተ «ገንዘቦቻችንና ቤተሰቦቻችን አስቸገሩን፤ ስለዚህ ምሕረትን ለምንልን፤» ይሉሃል፡፡ በልቦቻቸው ውስጥ የሌለውን ነገር በምላሶቻቸው ይናገራሉ፡፡ (አላህ) «በእናንተ ላይ ጉዳትን ቢሻ ወይም በእናንተ መጥቀምን ቢሻ ከአላህ (ለማገድ) ለእናንተ አንዳችን የሚችል ማነው? በእውነቱ አላህ፤በምትሠሰሩት ሁሉ ውስጥ ዐዋቂ ነው» በላቸው፡፡
M.Sadiq 48:11
12
ይልቁንም መልክተኛውና ምእመናኖቹ ወደ ቤተሰቦቻቸው ፈጽሞ አለመመለሳቸውን ጠረጠራችሁ፡፡ ይህም በልቦቻችሁ ውስጥ ተሸለመላችሁ፡፡ መጥፎንም መጠርጠር ጠረጠራችሁ፡፡ ጠፊዎች ሕዝቦችም ኾናችሁ፡፡
M.Sadiq 48:12
13
በአላህና በመልክተኛው ያላመነም ሰው እኛ ላከሓዲዎች እሳትን አዘጋጅተናል፡፡
M.Sadiq 48:13
14
የሰማያትና የምድር ንግሥናም የአላህ ነው፡፡ ለሚሻው ሰው ይምራል፤ የሚሻውንም ይቀጣል፡፡ አላህም መሓሪ አዛኝ ነው፡፡
M.Sadiq 48:14
15
ወደ ዘረፋዎች ልትይዟት በኼዳችሁ ጊዜ እነዚያ ወደ ኋላ የቀሩት ሰዎች «ተዉን እንከተላችሁ» ይሏችኋል፡፡ (በዚህም) የአላህን ቃል ሊለውጡ ይፈልጋሉ፡፡ «ፈጽሞ አትከተሉንም፡፡ ይህን (ቃል) ከዚህ በፊት አላህ ብሏል» በላቸው፡፡ ይልቁንም «ትመቀኙናላችሁ» ይላሉም፡፡ በእውነት እነርሱ ጥቂትን እንጅ የማያውቁ ነበሩ፡፡
M.Sadiq 48:15
16
ከአዕራቦች ወደ ኋላ ለቀሩት በላቸው፡- «የብርቱ ጭካኔ ባለቤት ወደ ኾኑ ሕዝቦች (ውጊያ) ወደ ፊት ትጥጠራላችሁ፡፡ ትጋደሏቸዋላችሁ፤ ወይም ይሰልማሉ፡፡ ብትታዘዙም አላህ መልካም ምንዳን ይሰጣችኋል፡፡ ከአሁን በፊት እንደ ሸሻችሁ ብትሸሹም አሳማሚን ቅጣት ይቀጣችኋል፡፡»
M.Sadiq 48:16
17
በዕውር ላይ (ከዘመቻ በመቅቱ) ኃጢአት የለበትም፡፡ በአንካሳም ላይ ኃጢአት የለበትም፡፡ በበሽተኛም ላይ ኃጢአት የለበትም፡፡ አላህንና መልክተኛውንም የሚታዘዝ ሰው ከሥሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸውን ገነቶች ያገባዋል፡፡ የሚሸሸውንም ሰው አሳማሚውን ቅጣት ይቀጣዋል፡፡
M.Sadiq 48:17
18
ከምእምናኖቹ በዛፊቱ ሥር ቃል ኪዳን በሚጋቡህ ጊዜ አላህ በእርግጥ ወደደ፡፡ በልቦቻቸውም ውስጥ ያለውን ዐወቀ፡፡ በእነርሱም ላይ እርጋታን አወረደ፡፡ ቅርብ የኾነንም መክፈት መነዳቸው፡፡
M.Sadiq 48:18
19
ብዙዎች ዘረፋዎችንም የሚወስዷቸው የኾኑን (መነዳቸው)፡፡ አላህም አሸናፊ ጥበበኛ ነው፡፡
M.Sadiq 48:19
20
አላህ ብዙዎችን ዘረፋዎች የምትወስዷቸው የኾኑን ተስፋ አደረገላችሁ፡፡ ይህችንም ለእናንተ አስቸኮለላችሁ፡፡ ከእናንተም የሰዎችን እጆች ከለከለላችሁ፡፡ (ልታመሰግኑትና) ለምእምናንም ምልክት እንድትኾን ቀጥተኛውን መንገድ ይመራችሁም ዘንድ (ይህንን ሠራላችሁ)፡፡
M.Sadiq 48:20
21
ሌላይቱንም በእርሷ ላይ ገና ያልቻላችኋትን አላህ ያወቃትን (ለእናንተ አዘጋጃት)፡፡ አላህም በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነው፡፡
M.Sadiq 48:21
22
እነዚያም የካዱት (የመካ ሰዎች በሑደይቢያ) በተወጉወችሁ ኖሮ ( ለሺሺት) ጀርባዎችን ባዞሩ ነበር፡፡ ከዚያም ዘመድም ረዳትም አያገኙም፡፡
M.Sadiq 48:22
23
አላህ ያችን ከዚህ በፊት በእርግጥ ያለፈችውን ልማድ ደነገገ፡፡ ለአላህም ልማድ ለውጥን አታገኝም፡፡
M.Sadiq 48:23
24
እርሱም ያ በመካ ውስጥ በእነርሱ ላይ ካስቻለችሁ በኋላ እጆቻቸውን ከእናንተ ላይ እጆቻችሁንም ከእነርሱ ላይ የከለከለ ነው፡፡ አላህም የምትሠሩትን ሁሉ ተመልካች ነው፡፡
M.Sadiq 48:24
25
እነርሱ እነዚያ የካዱ፣ ከተከበረው መስጊድም የከለከሏችሁ፣ መስዋእቱንም የታሰረ ሲኾን በስፍራው እንዳይደርስ (የከለከሉ) ናቸው፡፡ የማታውቋቸው የኾኑ ምእመናን ወንዶችና ምእምናት ሴቶች (ከከሓዲዎቹ ጋር) ባልነበሩ ያለ ዕውቀት እነርሱን መርገጣችሁና ከእነረሱ (በኩል) መከፋት የሚነካችሁ ባልኾነ ኖሮ (እጆቻችሁን ባላገድን ነበር) አላህ የሚሻውን ሰው በእዝነቱ ውስጥ ያገባ ዝንድ (እጆቻችሁን አገደ)፡፡ በተለዩ ኖሮ እነዚያን ከእነርሱ ውስጥ የካዱትን አሳማሚን ቅጣት በቀጣናቸው ነበር፡፡
M.Sadiq 48:25
26
እነዚያ የካዱት ደራይቱን የመሀይምነቲቱን ደራ በልቦቻቸው ውስጥ ባደረጉ ጊዜ (በቀጣናቸው ነበር)፡፡ አላህም በመልክተኛው ላይና በምእምናኖቹ ላይ እርጋታውን አወረደ፡፡ መጥጠበቂያይቱንም ቃል አስያዛቸው፡፡ በእርሷም ተገቢዎች ባለቤቶችዋም ነበሩ፡፡ አላህም በነገሩ ሁሉ ዐዋቂ ነው፡፡
M.Sadiq 48:26
27
አላህ ለመልክተኛው ሕልሙን እውነተኛ ሲኾን አላህ የሻ እንደ ኾነ ጸጥተኞች ኾናችሁ ራሶቻችሁን ላጭታችሁ፣ አሳጥራችሁም የማትፈሩ ስትኾኑ የተከበረውን መስጊድ በእርግጥ ትገባላችሁ፤ ያለውን በእርግጥ እውነት አደረገለት፡፡ (ከእርቁ) ያላወቃችሁትንም ነገር ዐወቀ፡፡ ከዚህም በፊት ቅርብን መክፈት አደረገ፡፡
M.Sadiq 48:27
28
እርሱ ያ መልክተኛውን በመሪ መጽሐፍና በእውነተኛ ሃይማኖት በሃይማኖት ሁሉ ላይ ሊያልቀው የላከ ነው፡፡ መስካሪም በአላህ በቃ፡፡
M.Sadiq 48:28
29
የአላህ መልክተኛ ሙሐመድ እነዚያም ከእርሱ ጋር ያሉት (ወዳጆቹ) በከሓዲዎቹ ላይ ብርቱዎች በመካከላቸው አዛኞች ናቸው፡፡ አጎንባሾች፣ ሰጋጆች ኾነው ታያቸዋለህ፡፡ ከአላህ ችሮታንና ውዴታን ይፈልጋሉ፡፡ ምልክታቸው ከስግደታቸው ፈለግ ስትኾን በፊቶቻቸው ላይ ናት፡፡ ይህ በተውራት (የተነገረው) ጠባያቸው ነው፡፡ በኢንጂልም ውስጥ ምሳሌያቸው ቀንዘሉን አንደአወጣ አዝመራና፣ (ቀንዘሉ) እንዳበረታው፣ እንደወፈረምና፣ ገበሬዎቹን የሚያስደንቅ ኾኖ በአገዳዎቹ ላይ ተስተካክሎ እንደ ቆመ (አዝመራ) ነው፡፡ (ያበረታቸውና ያበዛቸው) ከሓዲዎችን በእነርሱ ሊያስቆጭ ነው፡፡ አላህም እነዚያን ያመኑትንና ከእነርሱ በጎዎችን የሠሩትን ምሕረትንና ታላቅ ምንዳን ተስፋ አድርጎላቸዋል፡፡
M.Sadiq 48:29
Fetih suresi tamamlandı