1
የመጽሐፉ መወረድ አሸናፊው ጥበበኛው ከኾነው አላህ ነው፡፡
2
እኛ ወደ አንተ መጽሐፉን በእውነት (የተመላ) ሲኾን አወረድነው፡፡ አላህንም ሃይማኖትን ለእርሱ ብቻ ያጠራህ ኾነህ ተገዛው፡፡
3
ንቁ! ፍጹም ጥሩ የኾነው ሃይማኖት የአላህ ብቻ ነው፡፡ እነዚያም ከእርሱ ሌላ (ጣዖታትን) ረዳቶች የያዙት «ወደ አላህ ማቃረብን እንዲያቀርቡን እንጅ ለሌላ አንገዛቸውም» (ይላሉ)፡፡ አላህ በዚያ እነርሱ በእርሱ በሚለያዩበት ነገር በመካከላቸው ይፈርዳል፡፡ አላህ እርሱ ውሸታም ከሓዲ የኾነን ሰው አያቀናም፡፡
4
አላህ ልጅን መያዝ በፈለገ ኖሮ ከሚፈጥረው ውስጥ የሚሻውን ይመርጥ ነበር፡፡ ጥራት ተገባው፡፡ እርሱ አሸናፊው አንዱ አላህ ነው፡፡
5
ሰማያትንና ምድርን በእወነት ፈጠረ፡፡ ሌሊትን በቀን ላይ ይጠቀልላል፡፡ ቀንንም በሌሊት ላይ ይጠቀልላል፤ ፀሐይንና ጨረቃንም ገራ፡፡ ሁሉም ለተወሰነ ጊዜ ይሮጣሉ፡፡ ንቁ! እርሱ አሸናፊው መሓሪው ነው፡፡
6
ከአንዲት ነፍስ ፈጠራችሁ፡፡ ከዚያም ከእርሷ መቀናጆዋን አደረገ፡፡ ለእናንተም ከግመልና ከከብት፣ ከፍየል፣ ከበግ ስምንት ዓይነቶችን (ወንድና ሴት) አወረደ፡፡ በእናቶቻችሁ ሆዶች ውስጥ በሦስት ጨለማዎች ውስጥ ከመፍጠር በኋላ (ሙሉ) መፍጠርን ይፈጠራችኋል፡፡ ይህ ጌታችሁ አላህ ነው፡፡ ስልጣኑ የርሱ ብቻ ነው፡፡ ከእርሱ ሌላ አምላክ የለም፡፡ ታዲያ ወዴት ትዞራላችሁ፡፡
7
ብትክዱ አላህ ከእናንተ የተብቃቃ ነው፡፡ ለባሪያዎቹም ከህደትን አይወድም፡፡ ብታመሰግኑም፤ እርሱን ይወድላችኋል፡፡ ማንኛይቱም ኃጢኣትን ተሸካሚ ነፍስ የሌላይቱን ኃጢኣት አትሸከምም፡፡ ከዚያም መመለሻችሁ ወደ ጌታችሁ ነው፡፡ ትሠሩት የነበራችሁትንም ይነግራችኋል፡፡ እርሱ በልቦች ውስጥ ያሉትን ዐዋቂ ነውና፡፡
8
ሰውንም ጉዳት ባገኘው ጊዜ ጌታውን ወደርሱ ተመላሽ ኾኖ ይጠራል፡፡ ከዚያም ከእርሱ ዘንድ ጸጋን በሰጠው ጊዜ ያንን ከዚያ በፊት ወደርሱ ይጸልይበት የነበረውን (መከራ) ይረሳል፡፡ ከመንገዱ ለማሳሳትም ለአላህ ባላንጣዎችን ያደርጋል፡፡ «በክህደትህ ጥቂትን ተጣቀም፡፡ አንተ በእርግጥ ከእሳት ጓዶች ነህ» በለው፡፡
9
እርሱ የመጨረሻይቱን ዓለም (ቅጣት) የሚፈራ የጌታውንም ችሮታ የሚከጅል ሲኾን በሌሊት ሰዓቶች ሰጋጅና ቋሚ ኾኖ ለጌታው የሚግገዛ ሰው (እንደ ተስፋ ቢሱ ከሓዲ ነውን? በለው)፡፡ «እነዚያ የሚያውቁና እነዚያ የማያውቁ ይስተካከላሉን?» በላቸው፡፡ የሚገነዘቡት ባለ አእምሮዎቹ ብቻ ናቸው፡፡
10
(ጌታችሁ) «እናንተ ያመናችሁ ባሮቼ ሆይ! ጌታችሁን ፍሩ፡፡ ለነዚያ በዚህች በቅርቢቱ ዓለም መልካም ለሠሩት መልካም ምንዳ አላቸው፡፡ የአላህ ምድርም ሰፊ ናት፤ (ብትቸገሩ ተሰደዱ)፡፡ ታጋሾቹ ምንዳቸውን የሚሰጡት ያለግምት ነው» (ይላል) በላቸው፡፡
11
በል «እኔ አላህን ሃይማኖትን ለርሱ ያጠራሁ ኾኜ እንድግገዛው ታዘዝኩ፡፡
12
«የሙስሊሞችም መጀመሪያ እንድኾን ታዘዝኩ፡፡»
13
«እኔ ከጌታዬ ባምጽ የታላቁን ቀን ቅጣት እፈራለሁ» በል፡፡
14
አላህን «ሃይማኖቴን ለእርሱ ያጠራሁ ኾኜ እግገዛዋለሁ» በል፡፡
15
«ከእርሱ ሌላ የሻችሁትን ተገዙ፡፡ ከሳሪዎች ማለት እነዚያ በትንሣኤ ቀን ነፍሶቻቸውንና ቤተሰቦቻቸውን ያከሰሩ ናቸው፡፡ ንቁ! ይህ እርሱ ግልጽ ከሳራ ነው» በላቸው፡፡
16
ለእነርሱ ከበላያቸው ከእሳት የኾኑ (ድርብርብ) ጥላዎች አልሏቸው፡፡ ከበታቻቸውም ጥላዎች አልሏቸው። ይህ አላህ ባሮቹን (እንዲጠነቀቁ) በእርሱ ያስፈራራበታል፡፡ «ባሮቼ ሆይ! ስለዚህ ፍሩኝ፡፡»
17
እነዚያም ጣዖታትን የሚግገዟት ከመኾን የራቁ ወደ አላህም የዞሩ ለእነርሱ ብስራት አልላቸው፡፡ ስለዚህ ባሮቼን አብስር፡፡
18
እነዚያን ንግግርን የሚያዳምጡትንና መልካሙን የሚከተሉትን (አብስር)፡፡ እነዚያ እነርሱ አላህ የመራቸው ናቸው፡፡ እነዚያም እነርሱ ባለአእምሮዎቹ ናቸው፡፡
19
በእርሱ ላይ የቅጣት ቃል የተረጋገጠችበትን ሰው (ትመራዋለህን?) አንተ በእሳት ውስጥ ያለን ሰው ታድናለህን?
20
ግን እነዚያ ጌታቸውን የፈሩ ለእነርሱ ከበላያቸው የታነጹ ሰገነቶች ያሏቸው ሰገነቶች ከስሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸው የኾኑ አልሏቸው፡፡ (ይህንን) አላህ ቃል ገባላቸው፡፡ አላህ ቃሉን አያፈርስም፡፡
21
አላህ ከሰማይ ውሃን እንዳወረደና በምድርም ውስጥ ምንጮች አድርጎ እንዳስገባው አላየህምን? ከዚያም በእርሱ ዓይነቶቹ የተለያዩን አዝመራ ያወጣል፡፡ ከዚያም ይደርቃል፡፡ ገርጥቶም ታየዋለህ፡፡ ከዚያም ስብርብር ያደርገዋል፡፡ በዚህ ውስጥ ለባለ አእምሮዎች ግሣጼ አለበት፡፡
22
አላህ ደረቱን ለእስልምና ያስፋለትና እርሱም ከጌታው ዘንድ በብርሃን ላይ የኾነ ሰው (ልቡ እንደ ደረቀ ሰው ነውን?) ልቦቻቸውም ከአላህ መወሳት ለደረቁ ሰዎች ወዮላቸው፡፡ እነዚያ በግልጽ መሳሳት ውስጥ ናቸው፡፡
23
አላህ ከዜና ሁሉ መልካምን፣ ተመሳሳይ፣ ተደጋጋሚ የኾነን መጽሐፍ አወረደ፡፡ ከእርሱ (ግሣጼ) የእነዚያ ጌታቸውን የሚፈሩት ሰዎች ቆዳዎች ይኮማተራሉ፡፡ ከዚያም ቆዳዎቻቸውና ልቦቻቸው ወደ አላህ (ተስፋ) ማስታወስ ይለዝባሉ፡፡ ይህ የአላህ መምሪያ ነው፡፡ በእርሱ የሚሻውን ሰው ይመራበታል፡፡ አላህም የሚያጠመው ሰው ለእርሱ ምንም አቅኚ የለውም፡፡
24
በትንሣኤ ቀን ክፉን ቅጣት በፊቱ የሚመክት ሰው (ከቅጣት እንደሚድን ነውን?) ለበዳዮችም «ትሠሩት የነበራችሁትን (ቅጣቱን) ቅመሱ» ይባላሉ፡፡
25
ከእነሱ በፊት የነበሩት አስተባበሉ፡፡ ቅጣቱም ከማያውቁት በኩል መጣባቸው፡፡
26
አላህም በቅርቢቱ ሕይወት ውርደትን አቀመሳቸው፡፡ የመጨረሻይቱም ዓለም ቅጣት በጣም ትልቅ ነው፡፡ የሚያውቁ ቢኾኑ ኖሮ (አያስተባብሉም ነበር)፡፡
27
በዚህም ቁርኣን ውስጥ ለሰዎች ይገሠጹ ዘንድ ከየምሳሌው ሁሉ በእርግጥ አብራራን፡፡
28
መዛባት የሌለበት ዐረብኛ ቁርኣን ሲኾን (አብራራነው)፡፡ ሊጠነቀቁ ይከጀላልና፡፡
29
አላህ በእርሱ ተጨቃጫቂዎች የኾኑ ተጋሪዎች ያሉትን ባሪያና ለአንድ ሰው ብቻ ንጹሕ የኾነን ባሪያ (ለሚያጋራና ባንድነቱ ለሚያምን ሰው) ምሳሌ አደረገ፡፡ በምሳሌ ይስተካከላሉን? ምስጋና ለአላህ ይገባው፡፡ በእውነቱ አብዛኞቻቸው አያውቁም፡፡
30
አንተ ሟች ነህ፤ እነርሱም ሟቾች ናቸው፡፡
Sonraki 30 ayet →