2
ጥበብ በተመላበት ቁርኣን እምላለሁ፡፡
5
አሸናፊ አዛኝ ከሆነው አምላክ መወረድን ተወረደ፡፡
6
አባቶቻቸው ያልተስፈራሩትን ሕዝቦች ልታስጠነቅቅበት (ተወረደ)፡፡ እነርሱ ዘንጊዎች ናቸውና፡፡
7
በአብዛኞቻቸው ላይ ቃሉ በእውነት ተረጋገጠ፡፡ ስለዚህ እነርሱ አያምኑም፡፡
8
እኛ በአንገቶቻቸው ላይ እንዛዝላዎችን አደረግን፡፡ እርሷም (እንዛዝላይቱ) ወደ አገጮቻቸው ደራሽ ናት፡፡ እነርሱም ራሶቻቸውን ያንጋጠጡ ናቸው፡፡
9
ከስተፊታቸውም ግርዶን ከስተኋላቸውም ግርዶን አደረግን፡፡ ሸፈንናቸውም፡፡ ስለዚህ እነሱ አያዩም፡፡
10
ብታሰጠነቅቃቸውም ባታስጠነቅቃቸውም በእነርሱ ላይ እኩል ነው፡፡ አያምኑም፡፡
11
የምታስጠነቅቀው ግሳጼን የተከተለንና አልረሕማንን በሩቅ የፈራን ሰው ብቻ ነው፡፡ በምሕረትና በመልካም ምንዳም አብስረው፡፡
12
እኛ ሙታንን እኛ በእርግጥ ሕያው እናደርጋለን፡፡ ያስቀደሙትንም ሥራ ፈለጎቻቸውንም እንጽፋለን፡፡ ነገሩንም ሁሉ ገላጭ መሪ በኾነ መጽሐፍ ውስጥ አጠቃለልነው፡፡
13
ለእነርሱም የከተማይቱን (የአንጾኪያን) ሰዎች ምሳሌ መልክተኞቹ በመጧት ጊዜ (የኾነውን) ግለጽላቸው፡፡
14
ወደእነርሱ ሁለትን ሰዎች በላክንና ባስተባበሉዋቸው ጊዜ በሶስተኛም በአበረታንና እኛ ወደ እናንተ መልክተኞች ነን ባሏቸው ጊዜ (የኾነውን ምሳሌ ግለጽላቸው)፡፡
15
እናንተ መሰላችን ሰዎች እንጂ ሌላ አይደላችሁም፡፡ አልረሕማንም ምንም ነገር አላወረደም፡፡ እናንተ የምትዋሹ እንጂ ሌላ አይደላችሁም አሉዋቸው፡፡
16
(መልክተኞቹም) አሉ «ጌታችን ያውቃል፡፡ እኛ ወደእናንተ በእርግጥ መልክተኞች ነን፡፡
17
«በእኛ ላይም ግልጽ የኾነ ማድረስ እንጂ ሌላ የለብንም፡፡»
18
(ሕዝቦቹም) «እኛ በእናንተ ገደ ቢሶች ኾን፡፡ ባትከለከሉ በእርግጥ እንወግራችኋለን፡፡ ከእኛም አሳማሚ ቅጣት በእርግጥ ያገኛችኋል» አሉ፡፡
19
«ገደ ቢስነታችሁ ከእናንተው ጋር ነው፡፡ ብትገሰጹ (ትዝታላችሁን?) በእውነቱ እናንተ ወሰን አላፊዎች ሕዝቦች ናችሁ» አሏቸው፡፡
20
ከከተማይቱም ሩቅ ዳርቻ የሚሮጥ ሰው መጣ፡፡ «ወገኖቼ ሆይ! መልክተኞቹን ተከተሉ» አለ፡፡
21
«እነርሱ ቅኑን መንገድ የተመሩ ሲኾኑ ዋጋን የማየጠይቁዋችሁን ሰዎች ተከተሉ» (አላቸው)፡፡
22
«ያንንም የፈጠረኝን፤ ወደርሱም የምትመለሱበትን (ጌታ) የማልገዛ ለእኔ ምን አለኝ?» (አለ)፡፡
23
«ከእርሱ ሌላ አማልክትን እይዛለሁን? አልረህማን በጉዳት ቢሻኝ ምልጃቸው ከእኔ (ለመመለስ) ምንም አትጠቅመኝም፤ አያድኑኝምም፡፡
24
«እኔ ያን ጊዜ በግልጽ ስህተት ውስጥ ነኝ፡፡
25
«እኔ በጌታችሁ አመንኩ፤ ስሙኝም፤» (አለ)፡፡
26
«ገነትን ግባ» ተባለ፡፡ (እርሱም) አለ፡- «ወገኖቼ ቢያውቁ እመኛለሁ፡፡
27
«ጌታዬ ለእኔ ምሕረት ያደረገልኝና ከተከበሩትም ያደረገኝ መኾኑን፡፡»
28
ከእርሱም በኋላ በሕዝቦቹ ላይ (ልናጠፋቸው) ሰራዊትን ከሰማይ አላወረድንም፡፡ (በማንም ላይ) አወራጆችም አልነበርንም፡፡
29
(ቅጣታቸው) አንዲት ጩኸት እንጂ ሌላ አልነበረችም፡፡ ወዲያውኑም እነርሱ ጠፊዎች ኾኑ፡፡
30
በባሮቹ ላይ ዋ ቁልጭት! ከመልክተኛ አንድም አይመጣቸውም በእርሱ የሚሳለቁበት ቢኾኑ እንጅ፡፡
Sonraki 30 ayet →