Ana SayfaMealler › M.Sadiq and M.Sani Habib
MS

M.Sadiq and M.Sani Habib

M.Sadiq and M.Sani Habib
M.Sadiq and M.Sani Habib meali ile okumaya başla
Rum 1 / 60
1
አ.ለ.መ (አሊፍ ላም ሚም)፡፡
M.Sadiq 30:1
2
ሩም ተሸነፈች፡፡
M.Sadiq 30:2
3
በጣም ቅርብ በሆነችው ምድር፡፡ እነርሱም ከመሸነፋቸው በኋላ በእርግጥ ያሸንፋሉ፡፡
M.Sadiq 30:3
4
በጥቂት ዓመታት ውስጥ (ያሸንፋሉ)፡፡ ትዕዛዙ በፊትም በኋላም የአላህ ነው፡፡ በዚያ ቀንም ምእመናን ይደሰታሉ፡፡
M.Sadiq 30:4
5
በአላህ እርዳታ (ይደሰታሉ)፡፡ የሚሻውን ሰው ይረዳል፤ እርሱም አሸናፊው አዛኙ ነው፡፡
M.Sadiq 30:5
6
አላህ እርዳታን ቀጠረ፡፡ አላህ ቀጠሮውን አያፈርስም፡፡ ግን አብዛኛዎቹ ሰዎች አያውቁም፡፡
M.Sadiq 30:6
7
ከቅርቢቱ ህይወት ግልጹን ብቻ ያውቃሉ፡፡ እነርሱም ከኋለኛይቱ ዓለም እነርሱ ዘንጊዎች ናቸው፡፡
M.Sadiq 30:7
8
በነፍሶቻቸው (ሁኔታ) አያስተውሉምን? ሰማያትንና ምድርን በመካከላቸው ያለውንም ሁሉ አላህ በእውነትና በተወሰነ ጊዜ እንጂ አልፈጠራቸውም፡፡ ከሰዎቹም ብዙዎቹ በጌታቸው መገናኘት ከሓዲዎች ናቸው፡፡
M.Sadiq 30:8
9
በምድር ላይ አይኼዱምና የእነዚያን ከበፊታቸው የነበሩትን ሰዎች ፍጻሜ እንዴት እንደነበረ አይመለከቱምን? በኀይል ከእነርሱም ይበልጥ የጠነከሩ ነበሩ፡፡ ምድርንም አረሱ፡፡ (እነዚህ) ከአለሟትም የበዛ አለሟት፡፡ መልዕክተ ኞቻቸውም በተዓምራቶች መጡባቸው፤ (አስተባበሉምና ጠፉ)፡፡ አላህም የሚበድላቸው አልነበረም፤ ግን ነፍሶቻቸውን ይበድሉ ነበሩ፡፡
M.Sadiq 30:9
10
ከዚያም የእነዚያ ያጠፉት ሰዎች መጨረሻ በአላህ አንቀጾች በማስተባበላቸውና በእርሷ የሚሳለቁ በመኾናቸው ምክንያት መጥፎ ቅጣት ሆነች፡፡
M.Sadiq 30:10
11
አላህ መፍጠርን ይጀምራል፡፡ ከዚያም ይመልሰዋል፤ ከዚያም ወደርሱ ትመለሳላችሁ፡፡
M.Sadiq 30:11
12
ሰዓቲቱም በምትቆምበት ቀን አመጸኞች ጭጭ ይላሉ፡፡
M.Sadiq 30:12
13
ለእነርሱም ከሚያጋሩዋቸው (ጣዖታት) አማላጆች አይኖሯቸውም፤ በሚያጋሯቸውም (ጣዖታት) ከሓዲዎች ይኾናሉ፡፡
M.Sadiq 30:13
14
ሰዓቲቱ በምትቆምበት ቀንም በዚያ ቀን ይለያያሉ፡፡
M.Sadiq 30:14
15
እነዚያ ያመኑትና መልካሞችን ሥራዎች የሠሩትማ እነርሱ በገነት ጨፌ ውስጥ ይደሰታሉ፡፡
M.Sadiq 30:15
16
እነዚያም የካዱትማ በአንቀጾቻችንና በኋለኛይቱም ዓለም መገናኘት ያስተባበሉት እነዚያ በቅጣቱ ውስጥ የሚጣዱ ናቸው፡፡
M.Sadiq 30:16
17
አላህንም በምታመሹ ጊዜ በምታነጉም ጊዜ አጥሩት፤ (ስገዱለት)፡፡
M.Sadiq 30:17
18
ምስጋናም በሰማያትና በምድር ውስጥ ለርሱ ብቻ (የተገባው) ነው፡፡ በሰርክም፤ በቀትር ውስጥ በምትገቡም ጊዜ፤ (አጥሩት)፡፡
M.Sadiq 30:18
19
ሕያውን ከሙት ያወጣል፡፡ ሙታንም ከሕያው ያወጣል፡፡ ምድርንም ከሞተች በኋላ ህያው ያደርጋታል፡፡ እንደዚሁም (ከመቃብር) ትወጣላችሁ፡፡
M.Sadiq 30:19
20
እናንተንም ከዐፈር መፍጠሩ ከዚያም እናንተ ወዲያውኑ የምትበታተኑ ሰዎች መኾናችሁ ከአስደናቂ ምልክቶቹ ነው፡፡
M.Sadiq 30:20
21
ለእናንተም ከነፍሶቻችሁ (ከጎሶቻችሁ) ሚስቶችን ወደእነርሱ ትረኩ ዘንድ መፍጠሩ፣ በመካከላችሁም ፍቅርንና እዝነትን ማድረጉ ከአስደናቂ ምልክቶቹ ነው፡፡ በዚህ ውስጥ ለሚያስተውሉ ሕዝቦች ተዓምራቶች አልሉ፡፡
M.Sadiq 30:21
22
ሰማያትንና ምድርንም መፍጠሩ፣ የቋንቋዎቻችሁና የመልኮቻችሁም መለያየት፣ ከአስደናቂ ምልክቶቹ ነው፡፡ በዚህ ውስጥ ለዐዋቂዎች ተዓምራቶች አልሉበት፡፡
M.Sadiq 30:22
23
በሌሊትና በቀንም መተኛታችሁ፣ ከችሮታውም መፈለጋችሁ ከምልክቶቹ ነው፡፡ በዚህ ውስጥ ለሚሰሙ ሕዝቦች ተዓምራቶች አልሉበት፡፡
M.Sadiq 30:23
24
ብልጭታንም ፈሪዎችና ከጃዮች ስትሆኑ ለእናንተ ማሳየቱ፣ ከሰማይም ውሃን ማውረዱ፣ በእርሱም ምድርን ከሞተች በኋላ ሕያው ማድረጉ ከአስደናቂ ምልክቶቹ ነው፡፡ በዚህ ውስጥ ለሚያስቡ ሕዝቦች ተዓምራቶች አልሉበት፡፡
M.Sadiq 30:24
25
ሰማይና ምድርም (ያለምሰሶ) በትዕዛዙ መቆማቸው፣ ከዚያም (መልአኩ ለትንሣኤ) ከምድር ጥሪን በጠራችሁ ጊዜ እናንተ ወዲያውኑ የምትወጡ መሆናችሁ ከአስደናቂ ምልክቶቹ ነው፡፡
M.Sadiq 30:25
26
በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ የእርሱ ብቻ ነው፡፡ ሁሉም ለእርሱ ታዛዦች ናቸው፡፡
M.Sadiq 30:26
27
እርሱም ያ መፍጠርን የሚጀምር ከዚያም የሚመልሰው ነው፡፡ እርሱም (መመለሱ) በእርሱ ላይ በጣም ገር ነው፡፡ ለእርሱም በሰማያትም በምድርም ከፍተኛ ባሕርይ (አንድነትና ለእርሱ ብጤ የሌለው መኾን) አልለው፡፡ እርሱም አሸናፊ ጥበበኛ ነው፡፡
M.Sadiq 30:27
28
ለእናንተ ከነፍሶቻችሁ የሆነን ምሳሌ አደረገላችሁ፡፡ (እርሱም) እጆቻችሁ ከያዟቸው (ባሮች) ውስጥ በሰጠናችሁ ጸጋ ለእናንተ ተጋሪዎች አሏችሁን? ታዲያ እናንተና እነርሱ በእርሱ ትክክል ናችሁን? ነፍሶቻችሁን (ብጤዎቻችሁን) እንደምትፈሩ ትፈሯቸዋላችሁን? እንደዚሁ ለሚያስተውሉ ሕዝቦች፤ አንቀጾችን እንገልጻለን፡፡
M.Sadiq 30:28
29
ይልቁንም እነዚያ የበደሉ ሰዎች ያለ ዕውቀት ዝንባሌዎቻቸውን ተከተሉ፡፡ አላህም ያጠመመውን ሰው የሚያቀናው ማነው? ለእነርሱም ከረዳቶች ምንም የላቸውም፡፡
M.Sadiq 30:29
30
ወደ እውነት ተዘንባይ ኾነህም ፊትህን ለሃይማኖት ቀጥ አድርግ፡፡ የአላህን ፍጥረት ያችን አላህ ሰዎችን በእርስዋ ላይ የፈጠረባትን (ሃይማኖት ያዟት)፡፡ የአላህን ፍጥረት መለወጥ የለም፡፡ ይህ ቀጥተኛ ሃይማኖት ነው፡፡ ግን አብዛኛዎቹ ሰዎች አያውቁም፡፡
M.Sadiq 30:30