Ana SayfaMealler › M.Sadiq and M.Sani Habib
MS

M.Sadiq and M.Sani Habib

M.Sadiq and M.Sani Habib
M.Sadiq and M.Sani Habib meali ile okumaya başla
Nahl 1 / 128
1
የአላህ ትዕዛዝ መጣ፤ ስለዚህ አታስቸኩሉት፤ ከማይገባው ሁሉ ጠራ ከሚያጋሩትም ሁሉ ላቀ፤
M.Sadiq 16:1
2
ከባሮቹ በሚሻው ሰው ላይ መላእክትን ከራእይ ጋር በፈቃዱ ያወርዳል (ከሓዲዎችን በቅጣት) አስጠንቅቁ፤ እነሆ ከኔ በቀር ሌላ አምላክ የለም፤ ፍሩኝም ማለትን (አስታውቁ በማለት ያወርዳል)፡፡
M.Sadiq 16:2
3
ሰማያትንና ምድርን በእውነት ፈጠረ ከሚያጋሩት ሁሉ ጠራ፡፡
M.Sadiq 16:3
4
ሰውን ከፍትወት ጠብታ ፈጠረው፡፡ ከዚያም እርሱ ወዲያውኑ (ትንሣኤን በመካድ) ግልጽ ተከራካሪ ይኾናል፡፡
M.Sadiq 16:4
5
ግመልን፣ ከብትን፣ ፍየልንም በርሷ (ብርድ መከላከያ) ሙቀት ጥቅሞችም ያሉባት ስትኾን ለእናንተ ፈጠረላችሁ፡፡ ከርሷም ትበላላችሁ፡፡
M.Sadiq 16:5
6
ለእናንተም በእርሷ ወደ ማረፊያዋ በምትመልሷት ጊዜ በምታሰማሩዋትም ጊዜ ውበት አላችሁ፡፡
M.Sadiq 16:6
7
ጓዞቻችሁንም በነፍሶች ችግር እንጂ ወደማትደርሱበት አገር ትሸከማለች፡፡ ጌታችሁ በእርግጥ ሩኅሩኅ አዛኝ ነውና፡፡
M.Sadiq 16:7
8
ፈረሶችንም፣ በቅሎዎችንም፣ አህዮችንም ልትቀመጡዋቸውና ልታጌጡባቸው (ፈጠረላችሁ)፡፡ የማታውቁትንም ድንቅ ነገር ይፈጥራል፡፡
M.Sadiq 16:8
9
በአላህም ላይ (በችሮታው) ቀጥተኛውን መንገድ መግለጽ አለበት፡፡ ከእርሷም (ከመንገድ) ጠማማ አልለ፡፡ በሻም ኖሮ ሁላችሁንም በእርግጥ ባቀናችሁ ነበር፡፡
M.Sadiq 16:9
10
እርሱ ያ ከሰማይ ውሃን ያወረደ ነው፡፡ ከእርሱ ለእናንተ መጠጥ አላችሁ፡፡ ከእርሱም (እንስሳዎችን) በእርሱ የምታሰማሩበት ዛፍ (ይበቅልበታል)፡፡
M.Sadiq 16:10
11
በእርሱ ለእናንተ አዝመራን፣ (የዘይት) ወይራንም፣ ዘምባባዎችንም (ተምርን)፣ ወይኖችንም፣ ከፍሬዎችም ሁሉ ያበቅልላችኋል፡፡ በዚህ ውስጥ ለሚያስተነትኑ ሕዝቦች በእርግጥ ተዓምርአልለ፡፡
M.Sadiq 16:11
12
ለእናንተም ሌሊትንና ቀንን፣ ፀሐይንና ጨረቃንም ገራላችሁ፡፡ ከዋክብትም በፈቃዱ የተገሩ ናቸው፡፡ በዚህ ውስጥ ለሚያውቁ ሕዝቦች በእርግጥ ተዓምራቶች አልሉ፡፡
M.Sadiq 16:12
13
በምድርም ላይ መልኮቹ የተለያዩ ኾኖ ለእናንተ የፈጠረላችሁን ሁሉ (ገራላችሁ)፡፡ በዚህ ውስጥ ለሚገሰጹ ሕዝቦች በእርግጥ ተዓምር አልለ፡፡
M.Sadiq 16:13
14
እርሱም ያ ባሕርን ከእርሱ እርጥብ ስጋን ልትበሉና ከእርሱም የምትለብሱትን ጌጣጌጥ ታወጡ ዘንድ የገራ ነው፡፡ መርከቦችንም በውስጡ (ውሃውን) ቀዳጆች ኾነው (ሲንሻለሉ) ታያለህ፡፡ ከችሮታው ልትፈልጉና ልታመሰግኑም (ገራላችሁ)፡፡
M.Sadiq 16:14
15
በምድርም ውስጥ በእናንተ እንዳታረገርግ ተራራዎችን ጣለባት፡፡ ጂረቶችንም፣ መንገዶችንም ትመሩ ዘንድ (አደረገ)፡፡
M.Sadiq 16:15
16
ምልክቶችንም (አደረገ)፡፡ በከዋክብትም እነሱ ይምመራሉ፡፡
M.Sadiq 16:16
17
የሚፈጥር እንደማይፈጥር ነውን አትገሰጹምን
M.Sadiq 16:17
18
የአላህንም ጸጋ ብትቆጥሩ አትዘልቋትም፡፡ አላህ በእርግጥ መሓሪ አዛኝ ነውና፡፡
M.Sadiq 16:18
19
አላህም የምትደብቁትንና የምትገልጹትን ሁሉ ያውቃል፡፡
M.Sadiq 16:19
20
እነዚያም ከአላህ ሌላ የምትገዟቸው ምንንም አይፈጥሩም፡፡ እነርሱም ይፈጠራሉ፤
M.Sadiq 16:20
21
ሕያው ያልኾኑ ሙታን ናቸው፡፡ መቼ እንደሚቀሰቀሱም አያውቁም፡፡
M.Sadiq 16:21
22
አምላካችሁ አንድ አምላክ ብቻ ነው፡፡ እነዚያም በመጨረሻይቱ ዓለም የማያምኑት ልቦቻቸው ከሓዲዎች ናቸው፡፡ እነሱም የኮሩ ናቸው፤ (አያምኑም)፡፡
M.Sadiq 16:22
23
አላህ የሚደብቁትንና የሚገልጹትን ሁሉ የሚያውቅ ለመኾኑ ጥርጣሬ የለበትም፡፡ እርሱ ኩሩዎችን አይወድም፡፡
M.Sadiq 16:23
24
ለእነርሱም «ጌታችሁ (በሙሐመድ ላይ) ምንን አወረደ» በተባሉ ጊዜ «(እርሱ) የመጀመሪያዎቹ ሕዝቦች ተረቶች ነው» ይላሉ፡፡
M.Sadiq 16:24
25
(ይህንንም የሚሉት) በትንሣኤ ቀን ኀጢኣቶቻቸውን በሙሉ ከእነዚያም ያለ ዕውቀት ኾነው ከሚያጠሟቸው ሰዎች ኀጢአቶች ከፊሉን ሊሸከሙ ነው፡፡ ንቁ! የሚሸከሙት ኃጢኣት ምንኛ ከፋ!
M.Sadiq 16:25
26
እነዚያ ከእነሱ (ከቁረይሾች) በፊት የነበሩት በእርግጥ መከሩ፡፡ አላህም ሕንጻዎቻቸውን ከመሠረቶቻቸው አፈረሰ፡፡ ጣሪያውም በእነሱ ላይ ከበላያቸው ወደቀባቸው፡፡ ቅጣቱም ከማያውቁት ሥፍራ መጣባቸው፡፡
M.Sadiq 16:26
27
ከዚያም በትንሣኤ ቀን ያዋርዳቸዋል፡፡ እነዚያም «በእነሱ (ጉዳይ) ትከራከሩኝ የነበራችሁት ተጋሪዎቼ የት ናቸው» ይላቸዋል፡፡ «እነዚያ ዕውቀትን የተሰጡት ዛሬ ሐፍረቱና ቅጣቱ በእርግጥ በከሓዲዎች ላይ ነው» ይላሉ፡፡
M.Sadiq 16:27
28
(እነርሱ) «እነዚያ ነፍሶቻቸውን በዳይ ኾነው መላእክት የሚገድሏቸው ናቸው፡፡ ከክፉ ሥራ ምንም ነገር የምንሠራም አልነበርን» (ሲሉ) ታዛዥነታቸውን ይገልጻሉ፡፡ «በእውነት አላህ ትሰሩት የነበራችሁትን ነገር ዐዋቂ ነው» (ይባላሉ)፡፡
M.Sadiq 16:28
29
«የገሀነምንም ደጃፎች በውስጧ ዘውታሪዎች ስትኾኑ ግቡ» (ይባላሉ)፡፡ የኩሩዎችም መኖሪያ (ገሀነም) በእርግጥ ከፋች!
M.Sadiq 16:29
30
ለእነዚያም ለተጠነቀቁት «ጌታችሁ ምንን ነገር አወረደ» ተባሉ፡፡ «መልካምን ነገር» አሉ፡፡ ለእነዚያ ደግ ለሠሩት በዚሀች በቅርቢቱ ዓለም መልካም ኑሮ አላቸው፡፡ የመጨረሻይቱም አገር በእርግጥ በላጭ ናት፡፡ የጥንቁቆቹም አገር ምን ታምር!
M.Sadiq 16:30